የኤርትራው ፕሬዝዳንት ወደ ኢትዮጵያ ሊሄዱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 5/2010) የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በመጭው እሁድ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተነገረ።

የፕሬዝዳንት ኢሳያስ የኢትዮጵያ ጉብኝት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በ1990 ጦርነት ከተካሄደ ወዲህ የሚያደርጉት የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ይሆናል።

አቶ ኢሳያስ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ መድረክ ለተሰብሳቢዎች ንግግር እንደሚያደርጉ ከሰጠው ፕሮግራም ለመረዳት ተችሏል።

ለፕሬዝዳንቱ በደማቅ አቀባበል ለማድረግም የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ታውቋል።