የኢሳት ባልደረቦች ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2011) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሊቪዥንና ሬዲዮ ኢሳት ባልደረቦች ከአምስተርዳም፣ለንደንና ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ አሸኛኘት ተደረገላቸው።

ከዋሽንግተን ዲሲ የተነሱት የኢሳት ባልደረቦች ከዳላስ አይሮፕላን ማረፊያ ሲነሱ በኢትዮጵያውያን አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።

አሸኛኘቱን በስፍራው ተገኝቶ ሲዘግብ የነበረውም ምናላቸው ስማቸው ስለ አሸኛኘቱ መረጃውን ሊያደርሰን እዚህ ስቱዲዮ ይገኛል።