የአጋዚ ወታደሮች አንዲት ነፍሰጡር ሴት ገደሉ

የአጋዚ ወታደሮች አንዲት ነፍሰጡር ሴት ገደሉ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 02 ቀን 2010 ዓ/ም) በምስራቅ ሃረርጌ በቆቦ ከተማ ወታደሮች አንዲት የ3 ወር ነፍሰጡር ሴት መግደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አያንቱ ሙሃመድ የተባለችው የ21 አመት ሴት በወታደሮች ከተገደለች በሁዋላ አስከሬኗ መንገድ ላይ ወድቆ ተገኝቷል። የአንድ ልጆች እናት የሆነቸው አያንቱ ትናንት ምሽት አካባቢውን በሚጠብቁ ወታደሮች ታፍና ከተወሰደች በሁዋላ የመድፈር ሙከራ ተደርጎባት ሳትገደል እንዳልቀረች የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል።
ከግድያው ጋር በተያያዘ አንድ ወታደር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎአል።
በግድያው ዙሪያ የክልሉ መንግስት ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ሰዓት ድረስ የሰጠው መግለጫ የለም። ግድያው በርካታ ኢትዮጵያውያን አስቆጥቷል።