የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2011) የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ስራ አስፈጻሚ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ እየመከረ መሆኑ ተነገረ።

የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው ስብሰባ በአማራ ክልል ባሉ ፖለቲካዊና የህዝብ ችግሮች ጉዳይ ላይ ይመክራል ተብሏል።

በአጠቃላይ  በሃገራዊ ጉዳዮች ላይም እንደሚነጋገር ተገልጿል።

ህወሃት በቅርቡ ባካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የሃገሪቱ ጸጥታና ደህንነት እንዳሰባሰበውና ኢህአዴግ አስቸኳይ የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ እንዲጠራ እንደሚፈልግም አስታውቋል።

የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባም ትኩረት በሃገሪቱ የጸጥታ ጉዳይ ላይ ሊሆን እንደሚችልም ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።

በአሁኑ ጊዜ በምዕራብ ኦሮሚያ በኦነግ ታጣቂዎችና በመንግስት ጦር መካከል ግጭት መኖሩ ይነገራል።

በአካባቢው ከፍተኛ ፍተሻ እና እስር እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በሽሬ እንደስላሴ የመከላከያ ሰራዊቱ እንዳይንቀሳቀስ የአካባቢው ህዝብ እቀባና እገዳ መደረጉ ተሰምቷል።