የአቶ መለስ ዜናዊን ከዚህ አለም በሞት መለየት ተከትሎ በገዢው ፓርቲ አባላት ና በሰራዊቱ ውስጥ በስፋት የቀጠለው ስብሰባ አሁንም ተጠናክሮል

ህዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሳምንቱ መጀመሪያ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የፌድራል ፖሊስ አባላት የጋራ ስብሰባ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአፋር ክልል ተጀምሮዋል።

በአፋር ክልል በሎጊያ ከተማ አባሐና በተባለው ሆቴል ባለፈው ቅዳሜ በተጀመረው ስብሰባ ከሻለቃ በላይ ማእረግ ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችና የፌድራል ፖሊስ ሀላፊዎች መገኘታቸውን ከስፍራው የመጣው ዜና ያብራራል ። በአፋር ክልል ያለው አለመረጋጋትና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ዓብይ ትኩረት መሆኑ ተሰምቶዋል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚካሄደው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ በአፋር ክልልም ተጠናክሮ መቀጠሉ ተጨማሪ የፀጥታ ሀይሎች በአካባቢዎች እንዲታዩ ምክንያት መሆኑም ተሰምቶዋል። የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በምህፃረ ቃሉ አርዱፍ በአካባቢው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግም ይታወቃል፣ አምና በርካታ ቱሪስቶች መታፈናቸው ይታወሳል።