የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በከፍተኛ ድምቀት ለመቀበል እያደረገ ባለው ዝግጅት ላይ ሕዝቡ ተባባሪ እንዲሆን አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪ አቀረበ።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በከፍተኛ ድምቀት ለመቀበል እያደረገ ባለው ዝግጅት ላይ ሕዝቡ ተባባሪ እንዲሆን አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪ አቀረበ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) የንቅናቄው የአቀባበል ኮሚቴ አባላት ፦“የናፍቆት መልዕክቶቻችንን እንቀበል”በሚል ርዕስ ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል በሰጡት መግለጫንቅናቄው “የመንግሥትና የፖለቲካ ሥልጣን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበትን፤ የሀገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገለፅበትን፤ማኅበራዊና የፖለቲካ ችግሮች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚፈቱበትን እና ዲሞክራሲያዊ ባህል የሚበለፅግበትን-ብሄራዊ የፖለቲካዊ ሥርዓትግንባታ” የማገዝ ተልዕኮ አንግቦ፤ በአገር ውስጥ በህቡዕ፣ በጎረቤት አገር በኤርትራ እና ኢትዮጵያዊያን በሚገኙባቸው አገራት በሙሉ በህቡዕና በግልጽ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን አውስተዋል።
ንቅናቄው ሁለገብ ትግልን የመረጠው በሁኔታዎች አስገዳጅነት እንጂ የሚፈልገው፣ አሳምሮ የሚያውቀው እና የሚናፍቀው በዜግነት ላይየተመሠረተ ሰላማዊ የፓለቲካ ፉክክር እንደሆነ በተጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱን ያወሱት አስተባባሪዎቹ፣የንቅናቄው አመራሮች ወደ ሀገር ለመግባት ጥቂት ሳምንታት ብቻ እንደቀራቸው አመልክተዋል።
“አሁን በሀገራችን እየታየ ያለው የለውጥ ጅምር፣ ንቅናቄያችን የታገለለት እና ሲናፍቀው የቆየውን በዜግነት ላይ የተመሠረተ ፓለቲካ እናበሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ የመንግሥት ሥልጣን የሚያዝበትን ሥርዓት እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔዎችን ለመፍጠር የሚያመቻችነው” ያለው አስተባባሪ ኮሚቴው ፤ “በመሆኑም በውጭ አገራት ይገኙ የነበሩ አመራሮቹ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡበት ጉዞ “ናፍቆት” ተብሎመሰዬሙን አስታውቋል።
የናፍቆት መልዕክተኞችን ለመቀበል ከተቋቋሙ ኮሚቴዎች መካከልም አንዱ የሆነውና ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል መግለጫ የሰጠው ኮሚቴ ከዛሬጀምሮ የአቀባበል ስነ ስርአቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ድረስ የሚኖሩ የአቀባበል ተግባራትን እንዲያስተባበር ኃላፊነት መውሰዱ ተመልክቷል።
በዚህ ኮሚቴ ውስጥ የተካተቱትና ዛሬ መግለጫውን የሰጡት የኮሚቴ አባላት በነጻነት ትግሉ እሳት ተፈትነው ያለፉት – ብርሀኑ ተክለያሬድ፣ኤፍሬም ሰለሞን ፣ ኢየሩሳሌም ተስፋው እና ጥላሁን አበጀ ናቸው። እነኚሁ የነጻነት ታጋዮች የአቀባበል ኮሚቴው ከዛሬ ጀምሮ በይፋ ሥራውን መጀመሩን ባበሰሩበት በዛሬው መግለጫቸው ፤የንቅናቄው አመራሮች ወደሚናፍቁት አገርና የትግል ስልት ሲመለሱ የሚኖረው አቀባበል የደመቀ ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት ሁሉም ባለ ድርሻ አካላትእንዲተባበሯቸው፣ የንቅናቄውን አመራር አባላት ለመቀበል በተለያዩ መንገዶች ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ሁሉ ከኮሚቴው ጋር እንዲቀናጁ እና የመዲናዋ ሕዝብም በአቀባበሉ ላይ በመገኘት ለዲሞክራሲ ታጋዮች ያለውን ክብር እንዲገልፅ ጥሪ አቅርበዋል።
አስተባባሪ ኮሚቴዎቹ አክለውም የናፍቆት መልዕክተኞችን መግቢያ ቀንና ቀጣይ ፕሮግራሞችን በተከታታይ እንደሚገልጹ አሳውቀዋል።