የተጀመረው ሰላም እንዲቀጥል ካስፈለገ በስሜት መነዳት እንዲቆም አመራሩ የአሰራር ሂደቱን ማስተካከል አለበት ተባለ

የተጀመረው ሰላም እንዲቀጥል ካስፈለገ በስሜት መነዳት እንዲቆም አመራሩ የአሰራር ሂደቱን ማስተካከል አለበት ተባለ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ/ም ) የተለያዩ መድረኮች ሲካሄዱ በህብረተሰቡ ሚቀርቡ ጥያቄዎችን በመከታተል ምላሽ አለመሰጠቱ ፣በወጣቱ ዘንድ በስሜት የመነዳት ሁኔታ እንዲከሰት እያደረገ መሆኑን ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በተካሄደ ህዝባዊ ውይይት ላይ ተገልጿል።
ህብረተሰቡን ወደ ከፍተኛ ንዴትና ስሜት ውስጥ የሚያስገባው የአመራሩ ቸልተኝነት እንደሆነ የሚናገሩት አስተያዬት ሰጪ፣ የህዋሃት መሪዎች ከአሁን በፊት የህብረተሰቡን ጥያቄ በቸለተኝነት በመመልከት የክልሉ አመራሮች ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ፈለጋቸውን እንዲከተሉ በማድረግ የሰሩትን ስራ መድገም አይገባም ብለዋል።
አሁንም ህዝብን የሚያስቆጣን ነገር አመራሩ ለይቶ ማወቅና የሚከሰቱ ቸግሮችን በፍጥነት መፍታት ካልቻለ በስሜት የሚነዱ ወጣቶች በየጊዜው መፈጠራቸውና ለክልሉም ሆነ ለሃገሪቱ ስጋት እንደሆኑ አስተያዬት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡
አመራሩ ራሱን መፈተሸ አለበት የሚሉት አስተያዬት ሰጪ ወጣቱ በስሜት መነዳት እንዲያቆም ና የተጀመረው ሰላም አምዳጨልም ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡