የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት ክስ በደህንነት ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት እንዳይፈጸም ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011) የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት አቶ ድንቁ ደያስ በ11.3 ሚሊዮን ብር የቼክ ማታለል ወንጀል ተከሰው ታስረው እንዲቀርቡና ከሀገር እንዳይወጡ የፍርድ ቤት ቤት ትዛዝ ቢወጣባቸውም በደህንነት ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት ተፈጻሚ አለመሆኑን ምንጮች ገለጹ።

በኦሮሚያ ክልል ከትምህርት ዘርፍ በተጨማሪ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙት አቶ ድንቁ ደያስ ከገር እንዳይወጡ የፍርድ ቤት ትዛዝ ቢውጣባቸውም ውጭ ሐገር እንደሚመላለሱ ያገኘነው መረጃ  ያመለክታል።

አቶ አንተነህ ፈለቀ የተባሉ ግለሰብ በሳንዳፋ ኢንዱስትሪ ዞን የገነቡትን የወረቀትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶች ፋብሪካ በብር 28 ሚሊዮን ብር ለአቶ ድንቁ ደያሳ ይሸጣሉ።

በዚህ የሽያጭ ውል ስምምነት መሰርትም ከሽያጭ ዋጋው ወስጥ 3 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር የቅድሚያ ክፍያ ለአቶ አንተነህ ከተከፈላቸው በኋላ ቀሪውን 11 ሚሊዮን 395 ሺህ ብር ክፍያ ለመፈጸም አቶ ድንቁ ክወጋገን ባንክ ካላቸው ሂሳብ እንዲከፈል ቼክ ይሰጣሉ። ቀሪወን !3 ሚሊዮን 105 ሺህ የባንክ እዳውን እንዲችል ብሽያጭ ወሉ ተስማምተዋል።

አቶ አነተነህ የተሰጣቸውን ቼክ ይዘው ክፍያ ሲጠይቁ ግን በቂ ገንዘብ እንደሌለ ከባንኩ ይነገራቸዋል። አቶ ድንቁ ደያሳ ክፍያውን እንዲፈጽሙ በተደጋጋሚ በሽማግሌ ጭምር ቢጠየቁም ሊከፍሉ ባለመቻላቸው አቶ አንተነህ በፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸውን የመረጃ ምንጫችን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት አቶ ድንቁ ክሱ የተመሠረተባቸው ናፍያድ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚል ድርጅት ስም ከከፈቱት ሒሳብ አቶ አንተነህ ፈለቀ ለተባሉ ግለሰብ 11,395,000 ብር እንዲከፈል ለባንክ ቼክ በመጻፋቸውና በተጠቀሰው ሒሳብ ውስጥ በቂ ስንቅ ባለመገኘቱ መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡

የ11.3 ሚሊዮን ብር ዕዳ የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠርቶባቸዋል፡፡

አቶ ድንቁ ቼኩ በስማቸው የወጣ በመሆኑና በቼኩም ላይ የፈረሙት እሳቸው በመሆናቸው በቺክ ማታለል ወንጀልና  ክፍያው እንዲፈጸም ክሱ መቅረቡን ሰነዱ ያስረዳል፡፡

ከሳሽ አቶ አንተነህ ክሱን ያቀረቡት በሰበር መዝገብ ቁጥር 57923 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ መሠረት አቶ ድንቁ በቼኩ ላይ በመፈረማቸው ከማኅበሩ ጋር በአንድነትና በተናጠል ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ እንደሆነም ክሱ ያመለክታል፡፡

ክሱ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 21ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎትም፣ ተከሳሹ ሚያዝያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አቶ ድንቁ  ከሀገር እንዳይወጡ በፍርድ ቤት ትዛዝ ቢወጣባቸውም እርሳቸው ግን እንደልብ ወጭ ሀገር እንደሚመላለሱ ነው ለማወቅ የተቻለው።

በቂ ስንቅ የሌለው ቼክ የወንጀል ኃላፊነትን የሚያስከትል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ ግለሰቡ ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎትም ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ ትዕዛዝ ቢሰጥም በባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት ተፈጻሚ ሊሆን አልቻለም።

የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲው ባለቤት አቶ ድንቁ ደያሳ ከኦሮሚያ ባለስልጣናት በተለይም ከአቶ አባዱላ ገመዳ እና ሊሎችም ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል።