ኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተያዘው ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባን እንደሚጎበኙ ፎርቹን ዘገበ።

ኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተያዘው ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባን እንደሚጎበኙ ፎርቹን ዘገበ።
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ሳምንት አስመራን መጎብኘታቸው ይታወቃል።
በዚሁ የአስመራ ጉብኝት እጅግ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ዶክተር አብይ ከኤርትራው አቻቸው ከፕረኤዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጉብኝት፣ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1998 ዓመተ ምህረት ከሁለቱ አገራት ጦርነት ዋዜማ ማለትም ከ20 ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት ይሆናል።”
የኤርትራው ፕሬዚዳንት በጉብኝታቸው በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ለሕዝብ ንግግር እንደሚያደርጉ የዝግጅቱን መርሀ ግብር በመጥቀስ ጋዜጣው አስነብቧል።