አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲታወስ የሚል የውይይት መድረክ አዲስ አበባ ላይ ተዘጋጀ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲታወስ የሚል የውይይት መድረክ አዲስ አበባ ላይ ተዘጋጀ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 02 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰማያዊፓርቲ “አንዳርጋቸው ጽጌ ሲታወስ” በሚልርዕስ ግንቦት4 ቀን 2010ዓም የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። በውይይቱ ላይ መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በእንግድነት ተጋብዛለች ። ውይይቱ አምባሳደር ሲኒማ አካባቢ በሚገኘው የሰማያዊፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ ከጠዋቱ 8፡30-11፡00 ሰዓት ይካሄዳል።
አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈታ የሚጠይቀው የ3 ቀናት የማህበራዊ ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
በእለቱ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ዜጎች ወደ ሰማያዊፓርቲ ጽ/ቤት በመሄድ ውይይቱን እንዲካፈሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።