በኬንያ ምርጫ ኬንያታ በጠባብ ልዩነት እየመሩ ነው

የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት እስካሁን ባለው ቆጠራ የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዚዳንት ልጅ የሆኑት ኡሁሩ ኬንያታ በጠባብ ድምጽ እየመሩ ሲሆን፣ ምናልባትም በእርሳቸውና በሌላው ተቀናቃኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መካከል የድጋሜ ምርጫ ሊካሄድ ይችላል።

እስካሁን ባለው ቆጠራ ኬንያታ 50 በመቶ የሚሆን ድምጽ ቢያገኙም፣ ቆጠራው በቀጠለ ቁጥር ኦዲንጋ ልዩነቱን እያጠበቡ መምጣታቸው ይነገርላቸዋል።

ኬንያ የዘንድሮውን ምርጫ በሰላም ካጠናቀቀች በኬንያ ታሪክ ያለ ደም መፋሰስ የተደረገ የመጀመሪያው ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተብሎ ሊመዘገብ ይችላል።