በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለዶ/ር አብይ አህመድ የሚደረገው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለዶ/ር አብይ አህመድ የሚደረገው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 9 ቀን 2010 ዓ/ም )እሁድ እለት በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ ላይ ህዝቡ 1500 ሜትር እርዝመት ያለው ሰንደቃላማ በመያዝ የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር እየወሰደ ላለው አወንታዊ እርምጃ ድጋፉን ገልጿል። በዚህ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የወረዳ አስተዳዳሪው አቶ በጋሻው ተክሉ “አጥፍቻለሁና ይቅር በሉኝ” ብለው ህዝቡን ይቅርታ ጠይቀው፣ መስራት ለሚችል ሃላፊነታቸውን እንደሚለቁ ተናግረዋል።
በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ላይም ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ህዝቡ መንገድና መብራትን ጨምሮ ሌሎች የመሠረተ ልማት አግልገሎት እንዲሟላለት ጠይቋል።