በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢምባሲ ሰራተኞች ለአባይ ግድብ በዶላር አናዋጣም በማለት ያቀረቡት ተቃውሞ ምላሽ አገኘ

ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኞች በተለያዩ አገሮች ወደሚገኙ ኢምባሲዎች ሲላኩ በዶላርና በብር ይከፈላቸዋል። ይህን ተከትሎም የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ሰራተኞቹ ለአባይ ቦንድ ግዢ ቃል የገቡትን በዶላር እንዲከፍሉ መመሪያ ያወርዳል። የኢምባሲው ሰራተኞች በበኩላቸው ክፍያውን በብር እንጅ በዶላር እንደማይከፍሉ ተቃውሞዋቸውን ለውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለስልጣናት አቤት በማለት ተቃውሞአቸውን ገልጠዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የኢምባሲ ሰራተኞች ተቃውሞ ስጋት ላይ ስለጣለው፣ ሰራተኞች በዶላር መክፈላቸውን ትተው  በብር እንዲከፍሉ ትእዛዝ ሰጥቷል።

ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ መዋጮ እንዲያዋጡ መገደዳቸው አሁን ከሚታየው የኑሮ ውድነት በበለጠ ኑሮቸውን እያቃወሰው መሆኑን ይናገራሉ። በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ተቃውሞአቸውን እየገለጡ ቢገኝም በመንግስት በኩል የሚሰጠው መልስ ግን አሁንም አሳዛኝ እንደሆነ ሰራተኞች ይናገራሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide