በማጀቴና አጣዬ በኦነግ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 30/2011) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ማጀቴና አጣዬ በኦነግ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት ተፈጸመ።

የአካባቢው ነዋሪዎች  ከኦነግ ታጣቂዎች ጥቃት ሊሰነዘርብን ይችላል በሚል ስጋት ከስፍራው እየለቀቁ መሆናቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው  ገልጸዋል።

በአጣየ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ከባድ መሳሪዎች በያዙ የኦነግ ታጣቂዎች በተከፈተው ጥቃት 15 ነዋሪዎች መገደላቸው ተገልጿል።

በአጣዬ በነበረው ጥቃት ምክንያት መንገዶች ተዘግተዋል።

በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎችን ወደ ህክምና ማዕከላት ለመውሰድ እንዳልተቻለም ነዋሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል።