ግሎባል አሊያንስ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች የ31ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2011) ዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግሎባል አሊያንስ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች የ31ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ግሎባል አሊያንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል የድጋፍ ገንዘቡን ለወርልድ ቪዥን ማስረከቡን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰበውን ገንዘብ ያስረከበው የዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ፕሬዝዳንት አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው።

የጌዲዮ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና ለማቋቋም ለተዘጋጀው ፕሮጀክት የሚውለውን ገንዘብ የወርልድ ቪዥን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር መረከባቸው ታውቋል።

ወርልድ ቪዥን ለፕሮጀክቱ ስራ ማስኬጃ 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር መስጠቱም ተመልክቷል።

የግሎባል አሊያንስ ፕሬዝዳንት አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ከአዲስ አበባ ለኢሳት እንደገለጸው ገንዘቡ ለተናቃዮቹ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን በማሟላት መደበኛ ህይወታቸውን እንዲጀምሩ የሚያደርግ ነው።