ዶ/ር ፍቀሩ ማሩና ጨምሮ የተወሰኑ እሰረኞች ተፈቱ

ዶ/ር ፍቀሩ ማሩና ጨምሮ የተወሰኑ እሰረኞች ተፈቱ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ክሳቸው የተነሳላቸው የህክምና ባለሙያውን ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ፣ አቶ አግባው ሰጠኝ፣ አቶ ሲሳይ ባቱ፣ ፋሲል አለማየሁ እና አቶ ከመደ ጨመዳ ከእስር ቤት ወጥተዋል።
በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ ከ38 ተከሳሾች መካከል በነፍስ ይከላከሉ ከተባሉት አራት ተከሳሾች ውጭ 26 ተከሳሾችም ክሳቸው መነሳቱ ይታወቃል። ይሁን እንጅ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ ፍቅረማርያም አስማማውን ጨምሮ ሌሎች 16 ተከሳሾች በፍርድ ቤት ውስጥ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ ወደ ዝዋይ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን እስከዛሬ አልተፈቱም።