ይህ ቀን እንዲመጣ መስዋዕትነት ለከፈሉ ዜጎች እውቅና ሊሰጥ ይገባል

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011)በጨቋኙ መንግስት እስር ቤቶች እና የማሰቃያ ቦታዎች ቁም ስቅላቸውን ላዩ ጋዜጠኞች ፣ የመብት ተሟጋቾች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ይህ ቀን እንዲመጣ ለከፈሉት መስዋዕትነት ታላቅ ክብር እና እውቅና እንደሚገባቸው አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ገለጸ፡፡

አክቲቪስት ታማኝ በየነ በኢትዮጵያ ሆቴል በሽብርተኝነት ስም በእስር ለተንገላቱ ወገኖቹ የምስጋና እና የምሳ ገብዣ አድርጓል