የ2010 አጠቃላይ በጀት ውስጥ 100 ቢሊዮን ብር የሚሸፈነው በውጭ ብድርና ዕርዳታ እንደሚሆን ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009)

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መ/ቤት የ2010 ጠቅላላ የበጀት ወጪ 321 ቢሊዮን ብር አቀረበ። በጀቱ 54 ቢሊዮን ብር ጉድለት የታየበት ሲሆን፣ 100 ቢሊዮን ብር የሚሸፈነው በውጭ አገር እና በአገር ውስጥ ብድርና ዕርዳታ እንደሚሆን ተገልጿል።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ የ2010 የበጀት ዕቅዱን ለፓርላማ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከተያዘው አመት ጋር ያሉትን ልዩነቶች አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ከቀጣዩ አመት በጀት ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ በያዝነው የ2009 አመት 12 ቢሊዮን ብር የነበረው በ2010 ወደ 7 ቢሊዮን ብር እንዲቀንስ የተደረገ ሲሆን፣ በተቃራነው የመከላከያ በጀት ከ11 ቢሊዮን ወደ 12 ቢሊዮን ብር ከፍ መደረጉ ተገልጿል።

የልማት በጀት ተቀንሶ ወደ መከላከያ መጨመሩ ያነጋገረ ሲሆን፣ ሃገሪቷ የገባችበት የጸጥታ ስጋት እየጨመረ መሄዱን እንደሚያመለክት የዘርፉ ሙያተኞች ይገልጻሉ።