የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተወሰዱ

(ኢሳት ዲሲ– መስከረም 15/2011)

ባለፈውሳምንት ሰኞ ከአዲስ አበባ ታፍሰው ሰንዳፋ የነበሩ 36 የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታወቁ።

ፋይል

ትላንት ልጆቻቸውን ለመጠይቅ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተገኙት በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን መጠየቅ ሳይችሉ እዚያው አድረው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ለኢሳት እንደተናገሩትየማሰልጠኛው ጠባቂዎች ልጆቻቸው ስልጠና ላይ ስለሆኑ ሊያገኟቸው እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል ::

ይሁን እና ምን አይነት ስልጠና ላይ እንዳሉ የገለፁላቸው ነገር የለም::

ለልጆቻቸው የቋጠሩትን ስንቅም በአካባቢው ላገኟቸው የኔ ቢጤዎች መፅውተው ተመልሰዋል::

በአዲስ አበባ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፀ ወጣቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታፈሱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ ::