የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ ኢትዮጵያን ጎበኙ።

የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ ኢትዮጵያን ጎበኙ።
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ ዛሬ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። ሚስተር ኮንቴ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። መሪዎቹ-በሁለቱ አገራት የልማት ትብብር ስምምነቶች እንዲሁም በኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ሥምምነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል። ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ ነገ ወደ ኤርትራ በማቅናት በኤርትራና በጣሊያን የጋራ ግንኙነት፣ በቀጠናው እና በዓለም አቀፍ ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።