የጅማ ከተማ ህዝብ በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የጀግና አቀባባል አደረገ።

የጅማ ከተማ ህዝብ በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የጀግና አቀባባል አደረገ።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) እጅግ በርካታ የከተማዋ ህዝብ በጅማ ስቴዲየም ተገኝቶ አህመዲን ጀበልን የተቀበለው ሲሆን፣ ከህዝቡ የተዋጣውን የገንዘብ ስጦታም አበርክቶለታል። ኡስታዝ አህመዲን “ ከዚህ በሁዋላ ውሸታም መሪ፣ አስመሳይ አስተዳደር የኢትዮጵያ ህዝብ አይፈልግም። እኔ ሁሉንም ዘር ሃይማኖት ሳልለይ እውዳለሁ።
ኦሮሞ ነኝ፣ ሙስሊም ነኝ፣ ሰው ነኝ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ከሁሉም ፋር የምጋራቸው ነገሮች ስላሉ ሁሉንም እወዳለሁ። በዘር ፣ በብሄር፣ በሃይማኖት አንለያይም” በማለት የህዝቡን ስሜት የገዛ ንግግር አድርጓል። ኡስታዝ አህመዲን ይህንን ህዝብ ፍቅር እንጅ ክላሽ አይገዛውም ያለው አቶ አህመዲን፣ ባለፈው ተቃውሞ ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 20 ሺ ብር በአጠቃላይ 100 ሺ ብር ለግሷቸዋል።