የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 13/2011) የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ። https://www.ethiopiatrustfund.org/

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በይፋ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ በፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም የሚመራ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት አማካሪ ቦርድ መሰየሙም ይታወሳል።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት የሚኖሩ ችግረኛ ዜጎችን ለመደገፍ በቀን አንድ ዶላር እንዲያዋጡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተቋቋመው አማካሪ ቦርድ ትላንት በይፋ መርሃ ግብሩ መጀመሩን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት በአንድ ቀን ወደ 50ሺ የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡንም ለማወቅ ተችሏል።

ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ ዶት ኦርግ ላይ ገብተው ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።