የዛሬ ሳምንት ሰኞ ከአዲስ አበባ ታፍሰው ሰንዳፋ የነበሩ 36 የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታውቁ::

የዛሬ ሳምንት ሰኞ ከአዲስ አበባ ታፍሰው ሰንዳፋ የነበሩ 36 የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታውቁ::
( ኢሳት ዜና መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ/ም ) ትላንት ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተገኙት በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን መጠየቅ ሳይችሉ እዚያው አድረው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ለኢሳት እንደተናገሩት የማሰልጠኛው ጠባቂዎች ልጆቻቸው ስልጠና ላይ ስለሆኑ ሊያገኟቸው እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል :: ይሁን እና ምን አይነት ስልጠና ላይ እንዳሉ የገለፁላቸው ነገር የለም::
ለልጆቻቸው የቋጠሩትን ስንቅም በአካባቢው ላገኟቸው የኔ ቢጤዎች መፅውተው ተመልሰዋል::
በአዲስ አበባ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፀ ወጣቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታፈሱ መሆኑን መረጃዎችን ጠቅሶ ባልደረባችን ስለሺ ሽብሩ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።