የዘንድሮው ግንቦት 20 ካለፉት 27 ዓመታት በተለየ መልኩ ያለ ፉከራና ቀረርቶ ታስቦ ውሏል።

የዘንድሮው ግንቦት 20 ካለፉት 27 ዓመታት በተለየ መልኩ ያለ ፉከራና ቀረርቶ ታስቦ ውሏል።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) አገዛዙ በየዓመቱ ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር ህዝብን በተደጋጋሚ አሰልቺ ፕሮፓጋንዳ ሲያደነቁር የቆዬ ሲሆን ፣ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ስላለፈው ስርዓትም ሆነ ስለ ነጻነት ዕለትነቱ ፕሮፓጋንዳ ሳይነዛ እንዲያልፍ ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም በሰጡት መግለጫ “ዕለቱን የእረፍት እናድርገው” ከማለት ውጭ እስከዛሬ በሹመኞች ሲባል ስለቆዬው አሰልቺ ፕሮፓጋንዳ ምንም ሳይሉ አልፈዋል። ይህም የህወኃት አባላት የሆኑ ካድሬዎችን እንዳስቆጣቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚሰጧቸው አስተያዬቶች ለመረዳት ተችሏል።
በየዓመቱ ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር የህወኃት መገናኛ ብዙሀን “እምበር ተጋዳላይ” የሚል ጭፈራን ሲያስተጋቡ መኖራቸው ይታወቃል።