የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2011)የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪና መምህር የነበሩት የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት ተፈጸመ።

በስደትና በእስር ለበርካታ ዓመታት በኤርትራ ቆይተው ከወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ማክሰኞ ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ የቀብር ስነስርዓት በምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ መፈጸሙን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የአማራ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በመርዓዊ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የቀብር ስነስርዓታቸው የተፈጸመው ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ የስድስት ልጆች አባት እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።