የኪነጥበብ ባለሙያዎች በጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋል አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011)ከ30 በላይ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በጌዲዮ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኙ።

አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

ድምጻውያን፣የቲያትር ባለሙያዎች፣ ደራሲያንንና ሌሎች የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ያሳተፈው የልኡካን ቡድን አባላት ዜጎች ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።

የተፈናቀሉት ዜጎች ወደነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢሳት ያነጋገራቸው  የኪነጥበብ ባለሙያዎች ገልጸዋል።