የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) ከጥር እስከ ሚያዚያ 2003 ዓ/ም የአደረገው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

ሐምሌ 6 ቀን 2003 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) ከጥር እስከ ሚያዚያ 2003 ዓ/ም የአደረገው
የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ
በሃገራች በሥልጣን ላይ ያለው የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ በመረጃ ጨለማ ውስጥ ለመግዛት
ያሰፈነውን የአፈና ቀንበር ለመስበርና፣ ፍትህና ዴሞክራሲን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የኢትዮጵያ ሳተላይት
ቴለቪዥን የህዝብ አይንና ጆሮ በመሆን የበኩሉን አስተዋጾ ሲያደርግ መቆየቱን ይታወሳል።
እንደሚታወቀው ኢሳት በእቅድ ደረጃ በነበረበት እና ከዚያም በኋላ ለዓየር በበቃበት የአስራ አምስት ወራት ጊዚያት
ውስጥ የነበረበትን ማንኛውንም የገንዘብ ወጭ የሸፈነው በሀገራችን የዴሞክራሲ ሥርዓት መመሥረት ያለውን ወሳኝነት
እና ለዚህም ሥርዓት መመስረት በሚደረገው ጥረት የነጻ ሚዲያ ሊሰጠው የሚችለውን ከፍተኛ እገዛ በተረዱ
ኢትዮጵያዊያን ነው።
ከጥር እስከ ሚያዚያ 2003 ዓ/ም የኢሳት ማኔጅመንት ባደረገው አለም ዓቀፍ ዘመቻ አንድ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር
ለማሰባሰብ አቅዶ የነበረ ሲሆን፤ ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ይህንን ዕቅዱን ማሰባሰብ ባይችልም፤ በመላው ዓለም
በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ $300,132 (ሶስት መቶ ሺ አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት የአሜሪካ ዶላር)
በፕሌጅና በጥሬ ገንዘብ ለማሰባሰብ ችሏል።
በዚህም ዘመቻ ወቅት በገንዘብ ድጋፍም ሆነ በተለያዩ ደረጃዎች ዘመቻውን በማስፈጸም በኩል ለአደረጋችሁት
አስተዋጽዖ እና ተሳትፎ፤ በመረጃ አቅርቦት አፈና በጨለማ ውስጥ እንዲኖር በተፈረደበት፣ ሆኖም ኢሳትን እንደ ዓይኑ
እና ጆሮው አድርጎ በሚያየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሥም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ይህም ሆኖ የተሰበሰበው ገንዘብ ኢሳት በየወሩ ከሚያስፈልገው ከፍተኛ ወጭ አንጻር ሲታይ ለረጅም ጊዜ የማይዘልቅ
በመሆኑ ሌሎች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥረቶችን ማድረግ እንዳለብን እንድትረዱልን እንፈልጋለን።
ኢሳት የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት እንዲችል ያልተቋረጠ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ይኖርበታል። ከላይ በዘመቻው
የተሰበሰበው ገንዘብ ኢሳት በየወሩ ከሚያስፈልገው ከፍተኛ ወጪ አንፃር ሲታይ ላለፉት ተከታታይ ወራት አገልግሎቱን
እንዲሰጥ ያስቻለው ቢሆንም በቀጣይ ለረጅም ጊዜ የሚያቆየው አይደለም። በዚህም መሠረት፣ ኢሳት አገልግሎቱ
ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ለማስቻል የአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ቀጣይ ድጋፍና እገዛ ይሻል። ይህንንም ለማስፈጸም
የሚያስችል ሌሎች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥረቶችን የምናደርግ መሆኑን እና በዚህም የተለምዶ ተሳትፎአችሁ እንዳይለየን
አበክረን እያሳሰብን፣ እስካሁን ላደረጋችሁልን ሁሉ በድጋሚ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
የኢሳት የነጻነት መንፈስ ለዘላለም ይኑር!!!
የኢሳት አስተዳደር
management@ethsat.com
www.ethsat.com