የኢሳት ጋዜጠኞች ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2011)የኢትዮጵያ ሳተለይት ቴሌቪዥንና ሬድዮ ኢሳት ጋዜጠኞች ነገ ሐሙስ የካቲት 7/ 2011 ከተለያዩ የዓለም ክፍል በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ ተገለጸ።

 

የጋዜጠኞቹን የአዲስ አበባ ጉዞ አስመልክቶም በአዲስ አበባ የሚገኘው የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ በእቴጌ ጣይቱ ሆቴል መግለጫ ሰቷል።

የአስተባባሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ሺበሺ መግለጫውን አስመልክቶ ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ የጨለማው ዘመን ብርሃን የነበረ፣ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ውለታ የዋለ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የኢሳት ባልደረቦች ከሃገራቸው ተገፍተው የወጡ ሲሆን አሁን ግን በወጡበት መልክ ሳይሆን በክብር እንቀበላቸዋለን ብለዋል የኮሚቴው አስተባባሪ።