የኢሬቻ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ በሰላም ተጠናቀቀ። የባገዳዎች የስልጣን ሽግግርም ተካሄደ።

የኢሬቻ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ በሰላም ተጠናቀቀ። የባገዳዎች የስልጣን ሽግግርም ተካሄደ።
( ኢሳት ዜና መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ/ም ) “ኢሬቻ ለፍቅርና ለአንድነት” በሚል መሪ ቃል በአደአ ሆራ አሰርዲ ሃይቅ የተከበረው ጥንታዊውና ባህላዊው የኢሬቻ ምስጋና በዓል በደማቅ ሁኔታ ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች እና ከውጭ አገር የመጡ እንግዶች በበዓሉ ላይ ተሳትፈዋል። ከጸጥታ አስከባሪዎች በተጨማሪ ”ቄሮ” እና ”ቃሬ” በመባል የሚታወቁት ወጣቶች ሰላም ከማስከበር ጀምሮ ጉዳተኞችን በመርዳት ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸው ታውቋል። ይህን ታሪካዊ በዓል በዓለም አቀፉ ቅርስነት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳር አቶ ለማ መገርሳ መግለጻቸው ይታወሳል።
በተጨማሪም በኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ዘንድ ከፍተኛ ስልጣን እርከን የሚባለውን የአባገዳ ስልጣን ላለፉት ስምንት ዓመታት የመሩትና በመላ ኢትዮጵያዊያን ትላቅ ክብር ያላቸው አባገዳ በየነ ሰንበቶ ስልጣናቸውን ለአባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሳ አስረክበዋል።