የአርበኞች ግንቦት7 የአቀባባል ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካከል 2ቱ ታሰሩ

የአርበኞች ግንቦት7 የአቀባባል ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካከል 2ቱ ታሰሩ
( ኢሳት ዜና መስከረም 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድና ወጣት መኮንን ለገሰ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ መኖሪያ ቤታቸው እንዲፈተሽ ተደርጓል። ፖሊሶች የጦር መሳሪያና ገንዘብ እንዳለ ተጠቁመው መምጣታቸውን ለቤተሰቦች ቢናገሩም፣ ምንም ነገር እንዳላገኙ ታውቋል። መንግስት ከሰመሞ ግጭት ጋር በተያያዘ ጠርጥሮ እንደያዛቸው ፖሊሶች ተናግረዋል። ፖሊስ ከአዲስ አበባና አዋሳኝ ከተሞች በርካታ ወጣቶችን በጥርጣሬ ይዟል።