የአማራ ክልል ልኡካን ኤርትራ ገቡ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2011) የአማራ ክልል ልኡካን ኤርትራ ገቡ።

የአማራ ልኡካን በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያይተዋል።

በአማራ ክልል አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ የተመራው የአማራ ልኡካን ቡድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ የሆኑትን አቡነ አብርሃምን የጨመረ ሲሆን የጎዞው አላማ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሆነም ተመልክቷል።

ቀደም ሲል በአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን የተመራ የልኡካን ቡድን በተመሳሳይ ወደ ኤርትራ መጓዙ ይታወሳል።

ይህ ቡድን ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ባቀረበው ግብዣ መሰረት የኤርትራው ፕሬዝዳንት አማራ ክልልን በቅርቡ ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።