የባስኬቶ ልዩ ወረዳና የመለኮዛ ወረዳ አመራሮች ከስልጣን ተነሱ

(ኢሳት ዲሲሚያዚያ 14/2011)በባስኬቶ ልዩ ወረዳና በመለኮዛ ወረዳ ለዜጎች መፈናቀል ምክንያት ናቸው የተባሉ አመራሮች ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የኢሳት ምንጮች ገለጹ።

ምንጮቹ እንደሚሉት አመራሮቹን ከስልጣን ማውረድ ብቻ ሳይሆን በቁጥጥር ስር እንዲውሉም ተደርጓል።

አመራሮቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተገለጸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የወረዳው አመራሮች ባነሱት የቀበሌ ይገባኛል ጥያቄ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሞከረ ነው መሆኑ ታውቋል።

ነገር ግን ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው ተመለሱ ከማለት ውጪ ስለተመቻቸላቸው ቅድመ ሁኔታ የተባለ ነገር የለም ብለዋል የኢሳት ምንጮች።