የሶማሊ ልዩ ሃይል ሚሊሺያዎች በአሮምያ ክልል አዋሳኝ ከተሞች በመግባት ጥቃት ፈጸሙ።

የሶማሊ ልዩ ሃይል ሚሊሺያዎች በአሮምያ ክልል አዋሳኝ ከተሞች በመግባት ጥቃት ፈጸሙ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ-ሶማሊ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ ፐሬዚዳንት አቶ አብዲ አሌ ሚሊሺያዎችን ወደ ጭናክስን በመላክ ቢያስን 4 ሰዎች እንዲገደሉ አድርጓል። ከ100 ያላነሱ ሰዎች አካባቢውን ጥለው ሲሸሹ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ደግሞ መቃጠላቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው አቶ አብዲ አሌ የፌደራል ባለስልጣናት እርሳቸውን ከስልጣን ለማውረድ የሚሞክ ከሆነ ጅግጅጋን ሞቃዲሾ እንደሚያደርጓት ሰሞኑት ከተለያዩ የክልሉ አመራሮች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ መዛታቸውን የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።