የመጀመሪያው የአፍሪካ ንግድና የፋይናንስ አለም አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2011)አዲስ አበባ የአፍሪካ ንግድና የፋይናንስ አለም አቀፍ ጉባኤን ለመጀመሪያ ጊዜ ልታስተናግድ መሆኑ ተሰማ።

የመጀመሪያ ነው የተባለውን አለም አቀፍ የአፍሪካ ንግድና ፋይናንስ አለም አቀፍ ጉባኤን የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋና ከሚገኘው Rescue shipping and investment Agency ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው መሆኑም ታውቋል።

በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን የሚወክሉ የመንግስት መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት፤የፖሊሲ አውጪዎች፤የትልልቅ ኩባንያዎች ባለቤቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይገኙበታል ተብሎም ይጠበቃል።

የአፍሪካ ህብረት፤የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፤የአፍሪካ ልማት ባንክ፤፤ኢኮዋስ፤ ሳዴክ እና የአፍሪካ ንግድና ልማት ባንክን የመሳሰሉ አህጉራዊ ተቋማትም በጉባኤው ላይ እንደሚገኙ ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጉባኤው በመጪው ሚያዚያ 3 እና 4 በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል።