የመውሊድ በአል ተከበረ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር /2010)የነብዩ መሀመድ 1 ሺ 492ኛው የልደት በአል በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ።

በአሉ በተለይም በኢትዮጵያ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ በድምቀት ተከብሯል።

በበአሉ ላይ የእምነቱ ተከታዮች በአሉን ሲያከብሩ የሰላም፣የፍቅርና የመቻቻል አስተምህሮቶችን በመጠበቅ ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል።

የነቢዩ መሀመድን አስተምህሮ ህዝበ ሙስሊሙ እርስ በእርሱ በመዋድድና በመረዳዳት ሊተገብረው እንደሚገባ በበአሉ አከባበር ላይ ተገልጿል፡፡

በአሉ በዚህ በአሜሪካም በተለያዩ አካባቢዎች በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ውሏል።