የህዝብ ተወካዮች የሁለት ኮሚሽኖች አመራሮችን ሹመት አጸደቀ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁለት ኮሚሽኖችን አመራሮች ሹመት አጸደቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቅራቢነት ለአመራሮቻቸው ሹመት የጸደቀላቸው ኮሚሽኖች የእርቅና ሰላም ኮሚሽንና የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ኮሚሽን ናቸው።

ካርዲናል ብርሃነየሱስና ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ የእርቅና ሰላም ኮሚሽን ኮሚሽነርና ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሲሾሙ፣ ዶ/ር ጣሰው ገብሬና ኡስታዝ አቡበክር አህመድ የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ኮሚሽን ኮሚሽነርና ምክትል ሆናው መሾማቸውን የደረሰን መረጃ አምልክቷል።

ሹመቶቹን የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ህወሃት የምክር ቤት አባላት በሙሉ መቃወማቸውም ታውቋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ ለኢሳት እንደገለጹት ለኮሚሽኖቹ እንቅስቃሴ የመተባበር ግዴታ የሁሉም ክልል መንግስታት ይሆናል።