የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከስልጣናቸው ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) የሀረሪ ክልልን ለ12 ዓመታት ያስተዳደሩት አቶ ሙራድ አብዱላሂ ከስልጣናቸው ተነሱ።

ፋይል

በምትካቸው አቶ ኦሪዲን በድሪ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው መሾማቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሀረሪ ገዢ ፓርቲ ሃብሊ ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብን ተከትሎ ከስልጣናቸው የተነሱት አቶ ሙራድ ቤተሰባዊ አስተዳደር በማስፈንና ደጋፊዎቻቸውን በዙሪያቸው በማሰባሰብ ሲወነጀሉ ቆይተዋል።

አቶ ሙራድ ከሃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ የተላለፈው ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆንም ለተተኪያቸው አቶ ኦሪዲን ስልጣን አላስረክብም ብለው መቆየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።