ወጣቱ አፍሪካዊ ቢሊየነር ማስክ በለበሱ ታጣቂዎች ተጠለፈ።

ወጣቱ አፍሪካዊ ቢሊየነር ማስክ በለበሱ ታጣቂዎች ተጠለፈ።
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) ቢቢሲ የታንዛኒያ ፖሊስን ጠቅሶ እንደዘገበው የ43 ዓመቱ ቢሊየነር መሀመድ ደዋይ በዳሬሰላም ካረፈበት ሆቴል ነው የታገተው።
ቢሊየነር መሀመድ ደዋይ እንደወትሮው በዳሬሰላም ስዋነኪ ሆቴል ውጭ በሚገኝ ጅምናዚየም የማለዳ ስፖርት ሊሰራ ሲሄድ ነው ፊታቸውን የተሸፈኑ ታጣቂዎች ጠልፈው የወሰዱት።
ከወንጀሉ ጋር በተገናኘ ሶስት ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ሁለቱ አጋቾች የውጭ ዜጋ እንደሚሆኑ ፖሊስ ያለውን እምነት ገልጿል።
ወጣቱ ቢሊየነር መሀመድ ደዋይ የተጠለፈበት ምክንያት እስካሁን ግልጽ አይደለም።.
ፎርቢስ እንደተሰኘው ታዋቂው የቢዝነስ መጽሄት ሪፖርት የመሀመድ ደዋይ ሀብት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶለር የደረሰ ሲሆን፤ ከታንዛኒያ ብቸኛው ቢሊየነር ሆኖነ ተመዝግቧል።
ወጣቱ ቢሊየነር “ዙምባ”ተብሎ የሚጠራው የታንዛኒያ ታላቅ እግር ኳስ ክለብ ስፖንሰር መሆኑንም የበቢሲ ዘገባ ያመለክታል።