ከጋምቤላ ማረሚያ ቤት ያመለጡ 92 እስረኞች ሁለት ሰዎችን ገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2011)ከጋምቤላ እስር ቤት ከትላንት በስትያ ያመለጡ 92 እስረኞች ሁለት ሰዎችን ገደሉ።

በሌሎች ሶስት ሰዎች ላይም ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።

የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት በአኝዋክ ዞን ኢታንግ ወረዳ ላይ ጥቃት የፈጸሙት እስረኞችን ማን እንዳስታጠቃቸው የታወቀ ነገር የለም።

በሌላ በኩል በጋምቤላ  አኝዋክ ዞን ጆር ወረዳ አንድ ወታደራዊ ካምፕ መገኘቱን ለኢሳት በደረሰ መረጃ ላይ ተመልክቷል።

የተደራጁና ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ ሃይሎች የሚገኙበት ይህው ካምፕ በኢትዮጵያ መንግስት ስር እንዳልሆነ እየተነገረ ነው።

የአካባቢውን ነዋሪ ስጋት ውስጥ የከተተውን ወታደራዊ ካምፕ በተመለከተ የክልሉ መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት ሪፖርት ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።