ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር ማቋረጣቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር ማቋረጣቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ
( ኢሳት ዜና ጳግሜን 05 ቀን 2010 ዓ/ም ) በርካታ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ጋምቤላ መግባታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ በአኝዋኮች ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ ስለሚችሉ የመከላከያ አባላት እንዲያውቁት ይደረግ በማለት ጠይቀዋል።
ታጣቂዎች የማን ሃይል እንደሆኑ ነዋሪዎች ለመግለጽ አልቻሉም። ከዚህ በፊት ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ ታጣቂዎች ወደ ጋምቤላ ክልል በመግባት በርካታ ዜጎችን እያፈኑ ሲወስዱ ቆይተዋል።