ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ፣

የካቲት 2፣ 2003 ዓም
በዛሬው ዕለት የካቲት 2፣ 2003 ዓም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 5:45 ላይ ኢሳት ወደ
ኢትዮጵያና አካባቢ ሀገራት የሚያስተላልፈው የቀጥታ ፕሮግራም ስርጭት ተቋርጧል። የኢሳት ስራ
አመራር እና ቴክኒካል ቡድን ከታይኮም ኩባንያ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ፕሮግራሙ የተቋረጠበትን
ምክንያት ለማወቅ በመነጋገር ላይ ይገኛል።
ይህም በመሆኑ፦
ሀ) ከሳተላይት ኩባንያው ጋር ተነጋግረን የምናገኘውን ውጤት በአስቸኳይ ለህዝብ ይፋ እናደረጋለን።
ለ) የኢሳት ፕሮግራም የተቋረጠበት ምክንያት ምንም ይሁን ምን እስካሁን በቆየንበትም ሆነ
አስፈላጊም ከሆነ በሌላ ሳተላይት፣ ፐሮግራማችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማስተላለፋችንን
እንደምንቀጥል ከወዲሁ ማረጋገጥ እንወዳለን።
ሐ) ፕሮግራማችን ሙሉ በሙሉ ወደ አየር እስኪመለስ ድረስ በኢንተርኔት የምናስተላልፈው
ፕሮግራም የቀጠለ መሆኑን ለማስታወቅ እንወዳለን።
የኢሳት የነጻነት መንፈስ ለዘላለም ይኑር!!!
የኢሳት የበላይ ቦርድ፣