ኢትዮጵያ ለሁሉም የተመቸች ሃገር እንድትሆን እንሰራለን ተብሏል

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ/2011) ኢትዮጵያ ለሁሉም የተመቸች ሀገር እንድትሆንና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የለውጥ ሃይሉ ጠንክሮ እንደሚሰራ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለኢሳት ገለጹ።

በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሰሜን አሜሪካ ያካሄደውን ጉብኝት አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።

በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን አባላት የሰሜን አሜሪካ የጉዞ ዓላማ  ክልሉን በልማት፣በኢንቨስትመንት እና በሌሎችም ጉዳዮች ለማሳደግ የሚያግዝ ውይይት ማካሄድ  ነበር፡፡

ውይይቱም በአምስት የአሜሪካ ግዛቶች ተካሂዷል፡፡በዋሽንግተን ዲሲ የተጀመረው ውይይት በዳላስ በሲያትልና በሎስአንጀለስ እንዲሁም በአታላንታ ተካሂዷል።

የልዑካን ቡድኑ ከአማራ ተወላጆች እንዲሁም ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር በአምስት የተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ያደረገውን ውይይት አጠናቆ ትናንት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።

የቡድኑ አባላት ከዋሽንግተን ዳለስ አውሮፕላን ጣቢያ ሲነሱ ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው ጉዟአቸው እጅግ እጅግ የተሳካ እንደነበር ለኢሳት ገልጸዋል።

እንደ አቶ ገዱ ገለጻ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብውርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል። እናም ጥያቂያቸውን ለመፍታት  እንሰራለን ብለዋል።

ከልኡካን ቡድኑ ጋር የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ ስራአስፈጻሚና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማት አማካሪ ዶክተር አምባቸው መኮንን እንዲሁም በምክትል መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ መላኩ አለበል አብረው ነበሩ።

የአዴፓ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደም የዚሁ ጉብኝት አካል ነበሩ።

በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን አባላት ላለፉት 2 ሳምንታት በሰሜን አሜሪካ የነበራቸውን ጉዞ አጠናቀው ኢትዮጵያ ገብተዋል።