አዲሱ የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ቃለ መሃላ ፈጸሙ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ሮበርት ሙጋቤን የተኩት አዲሱ የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ኤምርሰን ናንጋግዋ ቃለ መሃላ ፈጸሙ።

ቀደም ሲል በሮበርት ሙጋቤ ከምክትል ፕሬዝዳንትነት የተባረሩት ኤመርሰን ናንጋግዋ በሕዝብ ግፊት ሕገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ የሀገሪቱ መሪ ሆነዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ በዚምባቡዌ ዲሞክራሲያዊ ስረአት እንደሚያሰፍኑና በሀገሪቱ አድልዎ የሌለበት የሁሉም ዜጎች ርዕሰ ብሔር እንደሚሆኑ ቃል መግባታቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል።