አንጋፋዋ ድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን ከዚህ አለም በሞት ተለየች

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 1/2010)አንጋፋዋ ድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በአዲስ አመት ዜማዋ እንቁጣጣሽ ይበልጥ የምትታወቀውና ትዝታ በፖስታና ሌሎች መሰል ታዋቂ የሙዚቃ ስራዎችን ለህዝብ ያደረሰችው አንጋፋዋ ድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን ባደረባት ሕመም ምክንያት ዛሬ ረቡዕ ረፋዱ ላይ በህክምና ላይ እያለች ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች።

ከ1949 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቲያትር፣በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ወይንም በብሔራዊ ቲያትር እንዲሁም በፖሊስ ሰራዊት ኦኬስትራ በድምጻዊነት ስታገለግል የቆየችው አንጋፋዋ አርቲስት ዘሪቱ ጌታሁን ላልፉት 61 አመታት በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ የራሳቸውን አሻራ ለጥበቡ ካበረከቱ አንጋፋዎች መካከል ድምጻዊት ዘሪቱ አንዷ ነበረች።

ኢሳት በአርቲስቷ ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለመላው ቤተሰቦቿ፣የጥበብ ጓደኞቿና አፍቃሪዎቿ መጽናናትን ይመኛል።