አንዳንድ የአዴፓ አመራሮች በሚከሰቱ ግጭቶች በቀጥታና በተዘዋዋሪ እጃቸው አለበት ሲል ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 12/2011)በአማራ ክልልና በአጎራባች አካባቢዎች በሚከሰቱ ግጭቶች አንዳንድ የአዴፓ አመራሮች በቀጥታና በተዘዋዋሪ እጃቸው አለበት ሲሉ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ዶክተር አምባቸው መኮንን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ግጭቶቹን ተከትሎ በተደረጉ ግምገማዎች የፓርቲ አንዳንድ አመራሮች በማባባስና ሰላም እንዳይፈጠር ማድረጋቸው ተደርሶበታል ብለዋል።

በአማራ ክልል የተስፋፋውን የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር ለማስቆም በየአካባቢው የፍተሻ ኬላዎችን በማቋቋም የመከላከል ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል ዶክተር አምባቸው።

ጽንፍ የረገጡ ቅስቀሳ የሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉና በሃገሪቱ ያለውን አብሮነት እንዳያሸረሽሩት እየታገልን ነው ብለዋል።