አቶ በረከት ስምዖን የአማራ ክልል ህግ የማስከበር አቅም አጥቷል አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 5/2011)አቶ በረከት ስምዖን የአማራ ክልል ህግ የማስከበር አቅም አጥቷል ሲሉ ተናገሩ።

ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመብኝ ነው ሲሉ በችሎት ተቃውሞ አሰሙ።

በዛቻና ማስፈራራት ምክንያት ጠበቃ የሚቆምልን አላገኘንም በማለት መናገራቸውም ታውቋል።

ሌላኛው ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ የፈጸምኩት ወንጀል የለም በማለት የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።