አቶ መላኩ ፈንታ የአልማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011) አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር(አልማ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ በሕወሀት አገዛዝ ወቅት በሐሰት ተወንጅለው ላለፉት 5 አመታት በእስር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል።

ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ ያገኙት አቶ መላኩ ፈንታ ለእስር በባለስልጣናት የተዳረጉት የተሰወረ ቀረጥ እንዲከፈል በመታገላቸው እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል።

አቶ መላኩ ፈንታ የሃገሪቱን የጉምሩክና የታክስ አስተዳደር ስርዓትን ያሻሻሉና የቀየሩ አመራርም ናቸው፡፡፡

በአሁን ጊዜ በአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት አቶ መላኩ ፈንታ አሁን ደግሞ የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር(አልማ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡

አማራ አቀፍ ልማት ማህበርን ወይዘሮ ብስራት ጋሻው ጠና በዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲመሩት መቆየታቸው ይታወሳል፡፡