አምባሳደሮች ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማና አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ 8 ባለስልጣናት በአምባሳደርነት ተሾሙ።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ስምንቱ ተሿሚዎች በየትኛው ሃገር እንደሚወከሉ ዝርዝሩ ባይገለጽም ሹመቱን ግን ዛሬ ማግኘታቸው ታውቋል።

የደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸውን በቅርቡ የለቀቁትና የግብርና ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ፣አቶ አለማየሁ ተገኑ፣አቶ እሸቱ ደሴ፣አቶ አዛናው ታደሰ ከተሿሚዎቹ ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ።

አቶ ዮናስ ዮሴፍ፣አቶ ያለው አባተና አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ በተመሳሳይ ተሹመዋል።

ሹመቱን ተከትሎ አሁን በተለያዩ ሃገራት በስራ ላይ ያሉ አምባሳደሮች እንደሚጠሩ ይጠበቃል።