አልሸባብ ሁለት ግብረሰዶማዊያንን እና አንድ ለኢትዮጵያ መንግስት ሲሰልል ነበረ ያለውን ግለሰብ ገደለ

ጥር ፫ (ሦስት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ማክሰኞ እለት ጽንፈኛው ቡድን አልሸባብ 20 ዓመት ወጣት ኢሳቅ አብሽሮ እና የ15 ዓመት ታዳጊ አብዱረዛቅ ሸክ ዓሊ ግብረሰዶማዊ ምግባር ሲፈጽሙ በአልሸባብ ፖሊሲሶች ተይዘው ሞት ተፈርዶባቸው አንገታቸውን ተቀልተዋል። ከሁለቱ ወጣቶች በተጨማሪ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶን ስር ለሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ሲሰልል ነበር በማለት ሰኢድ መሀመድ ዓሊ የተባለ አንድ የአካባቢው ነዋሪ በሶማሊያዋ ቡዋሊ ከተማ ዓደባባይ ላይ ተገሏል። አልሸባብ  ግድያውን አስመልክቶ ”ለማኅበረሰቡ ጸያፍ እና ኢ-ግብረገባዊ ነውረኛ ድርጊቶች” ሲል መግለጫ ሰጥቷል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አልሸባብ እና አልቃኢዳ በሶማሊያ ውስጥ በተለይ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃቶችን አጠናክረው መቀጠላቸውን አንዶሉሲያ ሬዲዮን በመጥቀስ ዘኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል።