ተለማማጅ ሀኪሞችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ዛቻና ማስፈራራት እየተደረገብን ነው  አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011)ከትላንት ጀምሮ ስራ ያቆሙ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተለማማጅ ሀኪሞችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በአስተዳደር በኩል ዛቻና ማስፈራራት እየተደረገብን ነው ሲሉ ገለጹ።

ፋይል

ጥያቄአችንን የጥቅም ብቻ በማስመሰል የሚዲያ ዘመቻ እንዲከፈትብን ተደርጓል ሲሉ ዛሬ መግለጫ ሰተዋል።

በተቃውሞአቸውም እንደሚቀጥሉ ነው ያስታወቁት።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ የህክምና ባለሙያዎቹን ክስ አስተባብለዋል።

ከነገ ጀምሮ በስራ ገበታቸው ላይ በማይገኙ የህክምና ባለሙያዎች ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ ዳይሬክተሩ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።